''የዘመነ የንግድ ስርዓት ለላቀ ገቢ ዕድገት '' በሚል መሪ ሀሳብ ከንግዱ ማህበረሰብ ጋር ውይይት ተካሂዷል፤

--------

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በዛሬው እለት በ11ዱም ክፍለ ከተሞች ከንግዱ ማህበረሰብ ጋር "የዘመነ የንግድ ሥርዓት፣ ለላቀ ገቢ ዕድገት!" በሚል መሪ ቃል የደረጃ "ለ" ግብር ከፋዮችን ያሳተፈ የውይይት መድረክ ተካሂዷል፡፡

በመርሀ ግብሩ ላይ በከተማዋ የንግዱን ማህረሰብ ተሳትፎ የላቀ እንዲሆን በኢኮኖሚ፣ በማህበራዊ ጉዳዮች እና በፀጥታ ስራዎች እንዲሁም በመልካም አስተዳደር ተግባራት ዙርያ በንግዱ ዘርፍ የተመዘገቡ ዋና ዋና ስኬቶች እና ከአገልግሎት አሰጣጥ እና ከንግዱ ማህበረሰብ አኳያ ያጋጠሙ ተግዳሮቶች በሰነድ ቀርቦ ውይይት ተደርጓል፡፡

ህገ-ወጥ ንግድን በመከላከል ዘመናዊ የንግድ ስርዓት ማስፈን፣ የምርት አቅርቦትን በማሻሻል የዋጋ ግሽበትን መቀነስ እና ገበያን ማረጋጋት፣ ዘመናዊ፣ ፍትሃዊና በውድድር ላይ የተመሰረተ የንግድና የገቢ ስርዓት መዘርጋት፣ የገቢ አሠባሠቡን አጠናክሮ ማስቀጠል እና ሌሎችም ላይ መንግስት በትኩረት እንደሚሰራ በመድረኮቹ ተገልጿል፡፡

ገቢን ማሳደግ እና የህብረተሰቡን የልማት ጥያቄ ለመመለስ የንግዱ ማህበረሰብ ፤ ከመንግስት ጎን በመቆም አስፈላጊውን ድጋፍ በማድረግ እና ህጋዊ የንግድ ስርዓት በመከተል የንግድ ስርዓቱን ለማሻሻል በቁርጠኝነት እንደሚሰሩ የመድረኩ ተሳታፊዎች ገልጸዋል፡፡ 

ህግንና ሥርዓትን አክብረው የሚነግዱ ነጋዴዎች በሀገር ልማት ላይ ያላቸውን አዎንታዊ ሚና በተገቢው በመገንዘብ ህገወጥ ንግድን በመከላከል ላይ የድርሻቸውን እንዲወጡ ጥሪ ቀርቧል።

ለተጨማሪ መረጃ፦

👉 YouTube https://www.youtube.com/channel/UCagI4q5d_EtvTsajRXWnFjA

👉 Tik Tok https://vm.tiktok.com/ZM6jGNeFE/

👉 Telegram https://t.me/AAcommu

👉 Facebook https://www.facebook.com

👉 Website https://cityaddisababa.gov.et/

Share this Post