"በቻይና አስደናቂና ፈጣን እድገት ባስመዘገቡ ከተሞች የተሳካ የስራ ጉብኝት በማድረግ ላይ እንገኛለን፡፡

በሻንጋይ ጉብኝታችን ከከተማዋ ከንቲባ ጎንግ ዜንግ ጋር ባደረግነው ውይይት የሁለቱ ከተሞች እህትማማች ስምምነት ለመፈራረም እና ግንኙነታችንን ይበልጥ በማጠናከር በህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ፣ በንግድ፣ኢንቨስትመንት ፣በቱሪዝም፣ በቴክኖሎጂ ፈጠራና ሽግግር እንዲሁም በሌሎች ጉዳዮች ዙሪያ በጋራ ለመስራት ተስማምተናል።

በቆይታችንም የሻንጋይን ከተማ የትራንስፖርት ማኔጅመንት ፣ የቴክኖሎጂ ፈጠራ ፣ የሙዚየም አገልግሎት ፣ የቆሻሻ አስተዳደር ማዕከልን እና የሎጂስቲክ አገልግሎቶቻቸውን ጎብኝተናል፡፡

በጉብኝታችን ለሀገራችን ከተሞች የሚጠቅሙ ጠቃሚ ሀሳቦችንና ልምዶችን ያገኘን ሲሆን በተለይም አዲስ አበባ ለሌሎች ከተሞች ተምሳሌት የማድረግና አለማቀፍ ተወዳዳሪነት አቅም በመፍጠር እያስመዘገብን ያለነውን ለውጥ ለማጠናከር የሚያግዙ ናቸው፡፡

ዓለም አቀፍ ተሞክሮዎችን ከከተሞቻችን ተጫባጭ ሁኔታ ጋር በማጣጣም አዲስ አበባ ለነዋሪዎቿ ምቹና ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ ለማድረግ በገባነው ቃል መሰረት በላቀ ትጋት ማገልገላችንን እንቀጥላለን!"

ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ለተጨማሪ መረጃ፦

👉 YouTube https://www.youtube.com/channel/UCagI4q5d_EtvTsajRXWnFjA

👉 Tik Tok https://vm.tiktok.com/ZM6jGNeFE/

👉 Telegram https://t.me/AAcommu

👉 Facebook https://www.facebook.com

👉 Website https://cityaddisababa.gov.et/

Share this Post