---------------
የከተማ አስተዳደሩ ገቢ በየዓመቱ እያደገ በመምጣቱ የሚሰሩ ፕሮጀክቶችና የመሰረተ ልማት አውታሮች ዝርጋታ፣ በትምህርት ዘርፍና በጤናው፣ በሰው ተኮር ስራዎች እንዲሁም፣ በከተማ ውበት እና በሌሎችም ዘርፎች ከተማዋ እያከናወነች ያለው ሁሉን አቀፍ እና አካታች የልማት ስሬ እየጨመረ እንዲመጣ ምክኒያት ሆኗል።
በዛሬው እለትም እነዚህን ፕሮጀክቶች የንግዱ ማህበረሰብ ተወካዮች ተዘዋውረው የጎበኟቸው ሲሆን ለሚ እንጀራ ማዕከል፣ የተስፋ ብርሀን የምገባ ማዕከላት ፣ የእንስሳት ልህቀት ማዕከል፣ የለሚ ኩራ የግብርና ምርቶች የገበያ ማዕከል፣ አድዋ ዜሮ ኪሎ ሜትር ሙዚየም፣ መንገዶች እና ተሻጋሪ ድልድዮች ከተጎበኙት መካከል ይጠቀሳሉ።
እነዚህ ፕሮጀክቶችም የንግዱ ማህበረሰብ በታማኝነት በከፈለው ግብር የተገነቡ እና በተጨማሪም የከተማዋን ራዕይ በሚጋሩ አካኩካተሰ በበጎ ፈቃድ ተግባር እራሱ የንግዱን ማህበረሰብ ጨምሮ ባለሀብቶች ባደረጉት ድጋፋ የተገነቡ ናቸው።
ፕሮጀክቶቹ ሰፊ የስራ እድል በመፍጠር እንዲሁም በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማት ትልቅ አስተዋጾ እያደረጉ ያሉ ሲሆን፣ የከተማ አስተዳደሩ ከሚሰበሰበው ገቢ 60 በመቶ የሚሆነውን ለካፒታል እና ዘላቂ የልማት ስራዎች እያዋለ መሆኑም ለጎብኚዎቹ ገለፃ ተደርጓል።
ከተማዋ የምታመነጨውን ገቢ በአግባቡ ለመሰብሰብ እና የገቢ አሰባሰቡን በማዘመን አገልግሎቱን ማቀላጠፍ ከተማ አስተዳደሩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራው ያለ መሆኑም ተጠቁሟል።
ከከተማዋ የንግድ ማህበረሰብ ጋር "የዘመነ ንግድ ሥርዓት ለላቀ ገቢ ዕድገት!" በሚል መሪ ሀሳብ ከወረዳ እስከ ክ/ከተማ ባሉ መድረኮች ውይይት ሲደረግ መቆየቱ የሚታወቅ ሲሆን በነገው እለትም በከተማ ደረጃ ይጠቃለላል።