በከንቲባ አዳነች አቤቤ የሚመራው የልዑካን ቡድን በቻይናዋ ሱቿን ግዛት ቼንዱ ከተማ የተለያዩ ቦታዎችን ተዘዋውሮ ጎብኝቷል፤

------------

የልዑካን ቡድኑ በሱቿን ግዛት እያደረገ በሚገኘው የስራ ጉብኝት የቻይና ከተሞች የተቀናጀ ልማት ጽንሰ ሀሳብን ተግባራዊ በማድረግ ገጠርን ከከተማ ጋር በማስተሳሰርና በተቀናጀ የልማት ስትራቴጂ የማልማት እንዲሁም የከተማ ግብርናን በማስፋፋት ረገድ በከተሞቻቸው የስራ ዕድል ከመፍጠር ባሻገር የግብርና ውጤቶችን ማትረፍረፍ የቻሉባቸውን ስራዎች በመመልከት በሀገራችን የተጀመረውን የሌማት ትሩፋት ይበልጥ ማስፋት የሚቻልበትን ልምድ ቀስሟል፡፡

በተጨማሪም የቻይና ከተሞች በጽዳትና ውበት እንዲሁም ከተሞች ለሰው ልጅ ተስማሚ ፣ ለቱሪዝም መስሕብ ፣ ለነዋሪዎች ለመኖሪያ ምቹ እንዲሁም በአካባቢ ጥበቃ የሰሯቸውን የተሳኩ ስራዎችን የልዑካን ቡድኑ ጎብኝቷል፡፡

በከንቲባ አዳነች አቤቤ የተመራው የልዑካን ቡድን በቻይና ከተሞች የነበረውን የስራ ጉብኝት አጠናቅቆ ወደ አዲስ አበባ ተመልሷል።

ለተጨማሪ መረጃ፦

👉 YouTube https://www.youtube.com/channel/UCagI4q5d_EtvTsajRXWnFjA

👉 Tik Tok= https://www.tiktok.com/@aacommu

👉 Telegram https://t.me/AAcommu

👉 Facebook https://www.facebook.com

👉 Website https://cityaddisababa.gov.et

Share this Post