27
Dec
2023
በከንቲባ ልዩ ወረዳ እየተሰጠ ባለው ስልጠና፣ የአዲስ አበባ ከተማ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ እናትዓለም መለሰ በሰጡት ማብራሪያ የተሳሳቱ የትርክት አስተሳሰቦችን ወደ ጎን በመተው ገዢ የሆነው ትርክት በመረዳት እንደ ሀገር አንድ በሚያደርጉን የወል ትርክቶች ላይ በትኩረት መስራት እንደሚገባ ተናግረዋል።
በተከታታይ እየተሰጡ ባሉ ስልጠናዎች ሀብት መፍጠር እና ማስተዳደር እንዲሁም በዛሬው እለት ገዢ ትርክት በሚሉ አጀንዳዎች ዙሪያ ሰፊ ውይይት ተደርጓል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ የሥነ-ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር አቶ አሰፋ ቶላ በበኩላቸው የብሔርተኝነት አሰተሳሰብን በሕብረ-ብሄራዊ ወንድማማችነት በመተካት እና ብሔራዊነትን በማጎልበትን አብሮነትን ማረጋገጥ ከፓርቲው አባላት ይጠበቃል ሲሉ ገልፀዋል፡፡
የልዩ ወረዳ ስልጠናው ለተከታታይ ሁለት ቀናት የሚቀጥል ሲሆን አዲዲስ ግንዛቤ የሚፈጥሩ ሰነዶች ቀርበው ውይይት የሚደረግባቸው ይሆናል።