27
Dec
2023
---------------
በአዲስ አበባ ከተማ አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ የቃሊቲ - ቱሉ ዲምቱ መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት አካል ሆነው እየተገነቡ ከሚገኙ ድልድዮች መካከል አንዱ የሆነው እና በቃሊቲ ማሰልጠኛ የቀለበት መንገድ መጋጠሚያ ላይ የተገነባው ተሸጋጋሪ ድልድይ ወደ ፍፃሜው ተቃርቧል፡፡
የማሳለጫ ድልድዩ 240 ሜትር ርዝመት ያለው ሲሆን፣ በቃሊቲ - ቱሉ ዲምቱ የመንገድ ፕሮጀክት ላይ ከሚገኙት ሦስት ድልድዮች መካከል ግዙፉ እና ሽንጠ ረጅሙ ነው፡፡
ይህ ድልድይ የቀድሞውን የቀለበት መንገድ አደባባይ ሳይነካ በቁመት ከፍ ብሎ የተገነባ በመሆኑ የትራፊክ እንቅስቃሴውን ከማሳለጥ ባሻገር ለአካባቢው ገፅታም ልዩ ውበት የሚያላብስ ሲሆን ከሳሪስ የሚመጣውን ትራፊክ ተቀብሎ ወደ ቃሊቲ የሚያሸጋግር ነው።