የከንቲባ ልዩ ወረዳ የአባላት እና አመራሮች ስልጠና ተጠናቀቀ፤

-----

በአዲስ አበባ ከተማ የከንቲባ ልዩ ወረዳ የፓርቲ አባላት "ከዕዳ ወደ ምንዳ" በሚል መሪ ሃሳብ በዓባላት ደረጃ ለተካታተይ አምስት ቀናት ሲሰጥ የቆየው ስልጠና በዛሬው እለት ተጠናቋል፡፡

ለአባላት የተሰጠው ስልጠናም በሃብት ፈጠራ፣ በገዥ ትርክቶች፣ በሰላም እሴት ግንባታ፣ በአገልጋይና ስልጡን ሲቪል ሰርቫንት ግንበታ ጉዳዮች ዙርያ ላይ ትኩረት ያደረገ ሲሆን አባላቱም ጠቃሚ ግንዛቤን የጨበጡበት ነው፡፡

ስልጠናው ሲጠናቀቅ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ጽ/ቤት በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የካቢኔ ጉዳዮች ምክትል ኃላፊ አቶ ግርማ ቤካ በሰጡት ማብራሪያ አባላቱ በመደመር እሳቤ ከልዩነት ይልቅ የጋራ የሚያደርጉንን ገዥ ትርክቶችን በማጉላት ሕብረ-ብሔራዊ አንድናታችንና ብልጽግናችንን ማረጋገጥ ይኖርብናል ሲሉ አሳስበዋል፡፡ 

በከተማችን ውጤታማ የሆነ አገልግሎት ለመስጠትም ተቋማትን በቴክኖሎጂ ለማዘመን እና ብቁ የሆነ የሰው ሃይል ለመፍጠር በትኩረት እየተሰራ መሆኑንም አቶ ግርማ ተናግረዋል፡፡

የስልጠናው የተሳታፉ የሆኑ አባላት በበኩላቸው በስልጠናው በቂ ግንዛቤ ማግነታቸውን ገልጸው ሕብረ-ብሄራዊ አንድነትን ለመገንባትና የወል ገዢ ትርክትን መሬት ለማስያዝ በሚደረገው ጥረት ሁሉ በቁርጠንነት ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውን በሰጡት አስተያየት ተናግረዋል፡፡

የከንቲባ ልዩ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ አባላት ከስልጠናው ማጠቃለያ በኃላ የአድዋ ዜሮ ኪሎ ሜትር ሙዚየም ፕሮጀክትን ጎብኝተዋል፡፡

Share this Post