በከንቲባ ጎሹ እንዳለማው የተመራው የባህር ዳር ከተማ ከፍተኛ አመራሮች ልዑካን ቡድን የዓድዋ ዜሮ ዜሮ ኪ/ሜ ሙዚየምን ጎብኝቷል::

በጉብኝታቸው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ታላቁ የዓድዋ ድል አባት አርበኞች የብሔርና የዕምነት ልዩነት ሳይገድባቸው ለሀገር ሉዓላዊነትና ነጻነት በአንድነት የመቆማቸውን ታሪክ የወል ትርክት በማድረግ ትውልድ እንዲማርበት ሙዚየሙ መገንባቱ ሌላ ታላቅ ታሪክ መሰራቱን ከንቲባ ጎሹ ገልጸዋል::

ከጉብኝቱ በኃላ ከንቲባ አዳነች አቤቤ የባህርዳር ከተማ አመራሮችን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው የተወያዩ ሲሆን የአዲስ አበባ ከተማ አመራር በመናበብ እና በመቀናጀት በርካታ ሰው ተኮር ስራዎችን እንዲሁም የከተማዋን ገፅታ የቀየሩ እና አዲስ አበባን የብልጽግና ተምሳሌት ለማድረግ ግዙፍ ፕሮጀክቶችን በመገንባት ለአገልግሎት ክፍት በማድረግ ላይ እንደሚገኝ በውይይቱ ወቅት ተናግረዋል::

Share this Post