ሕብረተሰቡ ለበዓል የሚፈልጋቸው ምርቶች አቅርቦት እጥረት እንዳያጋጥም እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ።

-------------

በአዲስ አበባ ከተማ በምክትል ከንቲባ ጃንጥራር አባይ የሚመራው የንግድ ቁጥጥርና የገበያ ማረጋጋት ግብረ ኃይል የግብይት ስርዓቱ ያለበትን ሁኔታ በመገምገም የቀጣይ አቅጣጫ አስቀምጧል።

በግምገማ መድረኩ ላይ ተገኝተው ውይይቱን የመሩት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጃንጥራር አባይ ምርት የሚያቀርቡ ድርጅቶችን እና የግብይት ቦታዎችን በመለየት የትስስር ሥራ መጀመሩን ገልፀዋል።

ለበዓል የሚያስፈልጉ ግብዓቶች በተመጣጣኝ ዋጋ ለነዋሪው ቅርብ በሆኑ የቅዳሜ ገበያዎች በኢግዚቪሽንና ባዛር እንዲቀርቡ እየተደረገ መሆኑንም ምክትል ከንቲባው ገልጸዋል።

የከተማ አስተዳደሩ በዓላቱን ምክኒያት በማድረግ በ11ዱም ክ/ከተሞች የሚገኙ ሁሉም እሁድ ገበያ መዳረሻዎች ከሰኞ እለት ጀምሮ በሁሉም አዘቦት ቀናት ለግብይት ክፍት እንዲሆኑ መወሰኑ ይታወቃል።

ለተጨማሪ መረጃ፦

👉 YouTube https://www.youtube.com/channel/UCagI4q5d_EtvTsajRXWnFjA

👉 Tik Tok= https://www.tiktok.com/@aacommu

👉 Telegram https://t.me/AAcommu

👉 Facebook https://www.facebook.com/profile.php?id=100066583024934...

👉 Website https://cityaddisababa.gov.et

Share this Post