04
Jan
2024
የተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮቹ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከተማውን ነዋሪ የኑሮ ጫና ለማቅለል እየሰራቸው ያሉ ስራዎች የበርካቶችን ሕይወት እየቀየሩ መሆናቸውን መገንዘባቸውን ገልፀዋል:: የዓድዋ ዜሮ ዜሮ ኪ/ሜ ሙዚየምን ጨምሮ በከተማዋ እየተገነቡ ያሉ ታላላቅ ፕሮጀክቶች የከተማዋን ገፅታ ከመቀየር ባሻገር ለትውልድ የሚተላለፉ ስራዎች መሆናቸውንም የተፎካካሪ ፖርቲ ተወካዮቹ ተናግረዋል::
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በበኩላቸው የከተማ አስተዳደሩ የነዋሪውን ሕይወት በዘላቂነት ለመቀየር ፣ ከተማዋን ለኑሮና ለስራ ምቹ ለማድረግ እንዲሁም የከተማችንን ገፅታ የሚቀይሩ በርካታ እቅዶችን ከነዋሪው ጋር በጋራ እየመከረ በመተግበር ላይ ይገኛል ብለዋል::
ለተጨማሪ መረጃ፦
👉 YouTube https://www.youtube.com/channel/UCagI4q5d_EtvTsajRXWnFjA
👉 Tik Tok= https://www.tiktok.com/@aacommu
👉 Telegram https://t.me/AAcommu
👉 Facebook https://www.facebook.com/profile.php?id=100066583024934&mibextid=ZbWKwL
👉 Website https://cityaddisababa.gov.et