06
Jan
2024
የቾንቺን ከተማ አስተዳደር ኮንግረስ ሊቀመንበር ዣዎ ሺቺንግ እና የልዑካን ቡድናቸው አዲስ አበባ ከበርካታ የቻይና ከተሞች ጋር በቅርበት እንደምትሰራ አስታውሰው፣ ከቾንቺን ከተማ ጋርም የእህትማማችነት ስምምነት እንድንፈራረም እና ግንኙነታችን ይበልጥ እንዲጠናከር ያላቸውን ፍላጎት መነሻ በማድረግ በኢኮኖሚ ትብብር፣ በቴክኖሎጂ ሽግግር፣ በቴክኒክና ሞያ፣ በነፃ የትምህርት እድል እንዲሁም በባህልና ቱሪዝም ዘርፎች ላይ በጋራ ለመስራት የሚያስችል የእህትማማችነት ስምምነት ለመፈራረም ተስማምተናል።"
ከንቲባ አዳነች አቤቤ