06
Jan
2024
“ታላቁ የዓድዋ ዜሮ ዜሮ ኪሎ ሜትር ሙዚየም የወል ትርክት ለሀገር አንድነት” በሚል ሀሳብ የፓናል ውይይት ተካሄደ።
በፓናል መድረኩ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤን ጨምሮ ሌሎች የከተማ አስተዳደሩ አመራሮች፣ ከክልሎች የመጡ የስራ ኃላፊዎች፣ የታሪክ ምሁራን እና የኪነ ህንጸ ባለሞያዎች እንዲሁም የሚዲያ አካላት ተሳትፈዋል።
የዓድዋ ድል በደም እና አጥንት የተገኘ ታላቅ ድል መሆኑን የተናገሩት ከንቲባ አዳነች ነገር ግን ይህ ታላቅ ድል ላለፉት ዓመታት በሚገባው ልክ አለመዘከሩን ገልጸዋል።
ዓድዋ የነጻነት አርማ የጥቁር ህዝቦች ሁሉ ድል ነው ያሉት ከንቲባ አዳነች ታላቁ የዓድዋ ዜሮ ዜሮ ኪሎ ሜትር ሙዚየም ታሪኩን በሚመጥን ልክ መገንባቱንም ተናግረዋል።
የዓድዋን ሙዚየም ገነባን ስንል ፕሮጀክት ብቻ ሳይሆን ታሪክም ጭምር ነው የገነባነው ያሉት ከንቲባ አዳነች፣ ገራዊ የጋራ ታሪካችንን እኩል ልንናገረው፣ እኩል ልንኮራበትም ይገባል ብለዋል።
በፓናል ውይይቱ የክልሎች ኮሙኒኬሽን ቢሮ እና የባህል እና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊዎች፣ የታሪክ ምሁራን፣ ስነ-ህንፃ ባለሞያዎች እና የሚዲያ አካላት ተሳትፈዋል።