ለመዲናዋ የሠላም ሠራዊት አባላት የአቅም ግንባታ ስልጠና መሰጠት ጀመረ፤

--------------

በሁሉም ክፍለ ከተሞች ለሰላም ሰራዊት አባላት እየተሰጠ ያለው የአቅም ግንባታ ስልጠና የመስክ ላይ ልምምድና የማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ የሰላም ማስከበር ቅንጅታዊ ተገባራት ላይ ማዕከል አድርጎ ለተከታታይ አምስት ቀናት የሚቆይ ነው ተብሏል።

 "የሰላም ሰራዊት አደረጃጀት ፀጥታን በማስተዳደር ሁለንተናዊ ለውጥ" በሚል መሪ ቃል ለ5ቀናት በሚቆየው በዚህ የሰላም ሰራዊት አባላት ስልጠና ላይ ከ11ዱም ክፍለ ከተሞች የተወጣጡ 11ሺህ 500 የሰላም ሰራዊት አባላት በ10 የስልጠና ማዕከላት ስልጠናቸውን በመውሰድ ላይ ናቸው።

የአቅም ግንባታ ስልጠናው ነዋሪው የሰላሙ ባለቤት እንዲሆን የሚያስችል ቅንጅታዊ አሰራር በመዘርጋት የከተማዋን ሁለንተናዊ ሰላም ማስጠበቅን ጨምሮ መዲናችን ከፊታችን ባሉ ቀናት የምታስተናግዳቸው የጥምቀት በዓል እና የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ፍጹም ሰላማዊነታቸው ተጠብቆ የሀገራችንንም ሆነ የከተማችንን በጎ ገጽታ ለዓለም አቀፉ ህብረተሰብ በሚያሳይ መልኩ እንዲፈፀሙ ማስቻልን ኢላማ ያደረገ መሆኑ ተመላክቷል።

Share this Post