አራራት ካራ ኮተቤ የመንገድ ማሻሻያ ፕሮጀክት ክረምቱ ተጠናክሮ ከመግባቱ በፊት ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት እንደሚሆን ተገለጸ ።

 

በም/ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ጥራቱ በየነ በተደጋጋሚ ከ ነዋሪዎች ቅሬታ የሚቀርበትን የአራራት ካራ ኮተቤ መንገድ ማሻሻያ ፕሮጀክት የደረሰበትን ደረጃ ጎብኝተዋል።ስራ አስኪያጁ የመንገዱ ፕሮጀክት በዲዛይን መቀየር፤ በወስን ማስከበር እና በተቋራጭ አቅም ችግር ተጓቶ እንደነበር በመግለፅ ከባለድርሻ አካላትና ከነዋሪዎች ጋር በመወያየትና ውሳኔ በመስጠት ተቋርጦ የነበረውን ስራ ለማጠናቀቅ በሚያስችል አቅም ክረምቱ ተጠናክሮ ከመግባቱ በፊት ተጠናቆ እንዲያልቅ አቅጣጫ መቀመጡን እና ወደ ተግባር መገባቱን ተናግረዋል፡፡

የአካባቢው ነዋሪዎች በበኩላቸው የመንገዱ ስራ ለረጅም አመት በመዘግየቱ ለኢኮኖሚና ለማህበራዊ ችግሮች ከ መዳረጋቸው በላይ በዕለት ዕለት እንቅስቃሴያቸው ከፍተኛ መተስተጓጉሎ እንደፈጠረባቸውም ተናግረዋል። ይሁን አንጂ አሁን ከፍተኛ አመራሩ ትኩረት ሰጥቶ ያለበትን ሁኔታ መገምገሙ የሚያስመሰግን ተግባር ነው ብለዋል።

የመንገዶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ኢ/ር ሞገስ ጥበቡ በበኩላቸው ፕሮጀክቱ በዋጋ ንረት እና የዲዛይን ማሻሻያ በመደረጉ ተጨማሪ በጀትና ጊዜ መውሰዱን ገልጸው መንግስት ተጨማሪ በጀት በመወስን ተቋርጦ የነበረውን ስራ ለማጠናቀቅና ለትራፊክ መንገድ ክፍት ለማድረግ በመሰራት ላይ መሆኑንና ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ እስካሁን ለተፈጠረው ችግር የአካባቢውን ነዋሪ ይቅርታ መጠየቁን ተናግረዋል ።

የየካ ክፍለ ከተማ ድርጀት ሃላፊ አቶ ታረቀኝ ገመቹ በ60 ቀናት ዕቅዳቸው ውስጥ የየካ የከተቤ መንገድ ፕሮጀክትና ሌሎች በህዝብ የተነሱ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት ከህብረተሰቡ ጋር በመወያየት በተገኘው ውጤት መሰረት አመራሩ ክትትልና ድጋፍ በማድረግ ላይ መሆኑን በጉብኝቱ ወቅት ተናግረዋል ።

Share this Post