በመድናዋ የከተማ ግብርናን የተሳካ በሚያደርጉት ጉዳዮች ላይ ውይይት ተካሄደ።

 

በአዲስ አበባ የተጀመረውን የተቀናጀ የከተማ ግብርና የልማት ስራዎች የተሳካ በሚያደርጉት ጉዳዮች ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ተካሂዷል።

የውይይቱ ተሳታፊዎች በቂርቆስ ክፍለ ከተማና በአዲስ አበባ ከተማ አከባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ቅጥር ጊቢ ውስጥ የለሙ የተቀናጀ የከተማ ግብርና እንቅስቃሴን የጎበኙ ሲሆን በተሰራው ስራ መደሰታቸውን ተናግረዋል።

የአከባቢ ጥበቃ ባለስልጣን በአንድ ወር ውስጥ የጓሮ አተክልት ንቅናቄ በማስጀመር ለሌሎች መሰል ተቋማት ትምህርትና ተሞክሮ መሆን በሚችል ደረጃ ና አበረታች ክንውን መሆኑን ጎብኚዎቹ ገልፀዋል።

አሁን ካለው ተጨባጭ ሁኔታ አንፃር በገጠር ከሚከናወነው የግብርና ስራ በተጨማሪ በከተማ ግብርና ትኩረት ሰቶ መስራት እንደሚገባ የውይይቱ ተሳታፊዎች አሳስበዋል።

በውይይቱ ከዚህ በፊት በሃገራችን ለከተማ ግብርና የተሰጠው ትኩረት አናሳ በመሆኑ በሚፈለገው መጠን ሳንጠቀምበት ቆይተናል ያሉት የአዲስ አበባ ከተማ አርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሸን ኮሚሽነር አቶ ባዬ ሽጉጤ የተጀመረውን የከተማ ግብርና ባለን ክፍት ቦታ ሁሉ በአግባቡ በመጠቀም ከራሳችን ፍጆታ አልፎ ለገበያ የሚሆን የምርት አቅርቦት ለማቅረብ ትኩረት ተሰጥቶት በስፋት እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ም/ኃላፊ አቶ ሁሴን ዝናብ በበኩላቸው ለከተማ ግብርና ሊውል የሚችል መሬት ለይቶ ከማዘጋጀት ባለፈ በትምህርት ቤቶች፣በመንግሥት መስሪያ ቤቶች፣በግለሰቦች መኖሪያዎችን ጨምሮ ሌሎችም አማራጮችን አሟጦ በመጠቀም የተቀናጀ የከተማ ግብርና ስራን ለማስፋት ታቅዶ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

Share this Post