የጌታችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ልደት በአል ምክንያት በማድረግ ቄራ በሚገኘው የተስፋ ብርሀን ቁጥር-5 የምገባ ማዕከል ወገኖቻችን ምሳ አብልተናል።

 

የከተማችን አመራሮችም በየክፍለ ከተማው በተገነቡ 20 የተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከላት ምሳ በማብላት አብረው እያከበሩ ይገኛሉ።

አረጋውያንና አቅመ ደካሞች እንዲሁም የሀገር ባለውለታ ወገኖቻችንን የኑሮ ሸክም እያቃለልን ክብርና ፍቅር እንድናጋራ አብራችሁን እየሰራችሁ ላላችሁ ባለብቶች ሁሉ መስጠት አያጎድልምና ፈጣሪ ይባርካችሁ!

መልካም የልደት በዓል!

ከንቲባ አዳነች አቤቤ

Share this Post