በየአመቱ እስከ 10ሺህ ለሚደርሱ በሴተኛ-አዳሪነትና በአስከፊ ህይወት የሚገኙ ሴት እህቶቻችንና ልጆቻችንን አሰልጥኖ የስራ ስምሪት የሚሰጥ "የተሃድሶ እና የክህሎት ማበልጸጊያ ማዕከል" ግንባታ ማስጀመርያ ስነስርት አካሂደናል፡፡

3.1 ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ በጀት የሚካሄድ ይህ ግንባታ ሁለንተናዊ ስልጠናና ክህሎት የሚሰጥበት የማሰልጠኛ ማዕከል ያለው ሲሆን ሴቶች በስነልቦናና በክህሎት ብቁ ሆነው እንዲወጡ ያስችላል።

ግንባታው የስልጠና ክፍሎች ፣የማደርያ ዶርሚተሪ የህፃናት ማቆያ ፣የመመገብያ ክፍሎች ፣መዝናኛዎች እና ሱቆች እንዲኖሩት ታስቦ የተሰራ ሁለገብ ማዕከል ነው፡፡

ሴቶች የማህበረሰብ መሰረት ናቸው ፤በማህበረሰቡ ውስጥ ስር በሰደዱ የተዛቡ አስተሳሰቦች እና ችግሮች ምክንያት ከሚያጋጥማቸው ማህበራዊ እክሎች በማላቀቅ ጠንካራ ማህበረሰብንና ትውልድን የመገንባት ስራ አንድ አካል ነው፡፡

ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን አብዝቶ ይባርክ!!

Share this Post