ከተወሰኑ ወራት በፊት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር አመራሮችን ሰብስበዎ ነበር። በስብሰባውም ለቀጣይ 100 ቀናት ዕቅድ ተግባራዊ የሚደረጉ ጉዳዮችን አቅጣጫ ማስቀመጣቸው ይታወሳል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በድጋሚ ዛሬ በጽሕፈት ቤታቸው የመስተዳድሩን አመራሮች አግኝተው የከተማውን 2014 በጀት ዓመት እና 2015 ሩብ ዓመት አፈጻጸም ገምግመዋል። በመጨረሻም በከተማዋ የተጀመሩ መልካም የልማት ሥራዎችን እንዲስፋፉ፤ ችግሮችም እንዲስተካከሉ አቅጣጫ ሰጥተዋል።

 

Share this Post