ከጊዜ ወደጊዜ ያየደገ በመጣው የህዝብ ቁጥር እድገትና የኢኮኖሚ እድገት የከተማችን አንዱ ጫና የሆነውን የትራንስፖርት አገልግሎት ለማቃለል ዘመናዊ የህዝብ መጓጓዣዎችን ወደ ሥራ እንደገቡ እየተደረገ መሆኑን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገልጸዋል።
የትራንስፖርት አገልግሎት ማቅረብ ብቻ ችግሩን ስለማይቀረፍ ለከተማችን ነዋሪዎች ምቹ የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲያገኝ የመንገድ መሰረተ ልማቱንም ለማሰፋት በየዓመቱ 8 ቢሊዮን ብር በመመደብ መንገድ እየተገነባ ነው ብለዋል::
ዛሬ ወደ አገልግሎት የገቡት አውቶቡሶች ዘመናዊ እና የነዋሪውን እንግልት የሚቀንሱ መሆናቸውን ገልፀዋል::
ከተማ አስተዳደሩ የህዝብ አውቶቡሶችን የትራንስፖርት ስምሪታቸውም ዘመናዊና የተሳለጠ እንዲሆን እየተገነባ ያለው ዘመናዊ የትራፊክ ማኔጅመንት ሲስተም በቅርቡ ይጠናቀቃል ብለዋል ::
የትራንስፖርት አገልግሎቱ ውጤታማ ለማድረግ የሰው ሃይሉ በታማኝነት እና በትጋት ማገልገል ይጠበቃል ብለዋል ::
ለህዝባችን ጫናን የሚቀንስ እንጂ ጫናን የሚጨምር ተግባር መፈፀም የለብንም ፤ ተነጋግረን የማንፈተው ተወያይተን የማንግባባበት ምንም አጀንዳ የለም ያሉት ከንቲባ አዳነች አቤቤ በመተባበር በመደጋገፍ ለለውጥ የምንተጋ እንሁን ሲሉም በአፅንአት ተናግረዋል::
አህጉራዊና ዓለማቀፋዊ ሃላፊነት ያሏት አዲስ አበባ ሃላፊነትዋን የምትወጣው በነዋሪዎቹ የጋራ ጥረት በመሆኑ የሁላችን ትጋት ለከተሞችን እድገት ያስፈልገናል ብለዋል ::
በአጭር ጊዜ በራሱ የውጭ ምንዛሬ 100 አውቶቡሶች ላቀርበው ብራይተን ትሬዲንግ አመስግነዋል ::
የትራንስፖርትና ሎጂስቲክ ሚኒስትር ዶ/ር ዓለሙ ስሜ አ/አበባ ከተማ በሚሰራቸው ሰው ተኮር ስራዎች እጅግ የሚደነቁ ናቸዉ ብለዋል ::
በተለይም ከተማችን እያጋጠማት ያለዉ የትራፊክ መጨናነቅ የህዝብ የትራስፖርቱን አገልግሎት ለማሻሻል ከተማ አስተዳደሩ የዜጎች በክብር ሳይንገላቱ የትራንስፖርት እንዲያገኙ የሚሰራቸው ስራዎች ከፍተኛ ውጤት ያመጡ ናቸው ብለዋል ::
አቶ ምትኩ አስማረ የአ/አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ሃላፊ ዛሬ ወደ አገልግሎት የገቡት 100 የከተማ አውቶቡሶች የከተማውን የትሪንስፖርት ሸፋን ያሳድጋል ፥ በቀጣይም የከተማውን ህዝብ የትራንስፖርት ፍላጎት ለማሟላት ስትራቴጅዎች ተነድፈው እየተሰሩ ነው ብለዋል።
የከተማ አስተዳደሩ በ3.8 ቢሊየን ብር ወጪ 2ዐዐ አውቶቡስችን ለማስገባት ከብራይተን ትሬዲንግ በተገባው ስምምነት 100 አውቶቡስች ዛሬ ወደ አገልግሎት እንዲገቡ ተደርጓል።