የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለቦረና የ 102 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ!

የከተማ አስተዳደሩ በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን ያጋጠመው ችግር ለክልሉ ብቻ የሚተው ጉዳይ ባለመሆኑ ለድርቅ ለተጋለጡ ወገኖቻችን የሚሆን ድጋፍ አድር::

በዚህም በከተማዋ የሚገኙ ባለሃብቶችን እና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን በማስተባበር 100 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ለማድረግ ወስኗል::

የስድስት ወራት የስራ አፈፃፀም ግምገማ ላይ የሚገኘው የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራር በበኩሉ የሁለት ሚሊዮን ብር ድጋፍ አድር::

የከተማ አስተዳደሩ በተለያዩ ጊዜያት በተለያዩ የሃገራችን ክፍሎች በሚያጋጥሙ ሰው ሰራሽ እና የተፈጥሮ ችግሮች በግንባር ቀደምትነት ድጋፍ ሲያደርግ መቆየቱ ይታወቃል::

Share this Post