07
Jan
2024
የተመረቁት ሁለቱ ባለ 11 ወለል ህንፃዎች በሶስት ወራት ጊዜ ተገንብተው የተጠናቀቁ ሲሆኑ በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር የ’መደመር ትውልድ መጽሃፍ ሽያጭ ገቢ እና ከኦቪድ ኮንስትራክሽን ግሩፕ ድጋፍ የተገነቡ ናቸው። ህንፃዎቹ ባለአንድ፣ ባለሁለት እና ባለሦስት የመኝታ ክፍሎች ያላቸው 110 ቤቶች እንዲሁም እታችኛው ወለል ላይ 51 የምድር ቤት ክፍሎችን የያዙ ናቸው።
በተጨማሪም የጋራ የእንጀራ እና ዳቦ መጋገሪያ፣ ማብሰያ እና የማጠቢያ አካባቢዎች የተካተቱባቸው ናቸው። ሁለቱ አፓርትመንቶች በጠባብ ቦታ ላይ ለየአገልግሎቱ በልዩ ሁኔታ የመጠቀም ጥበብ ያረፈባቸው ሲሆኑ፣ ሁሉም ቤቶች ሙሉ እቃ ተገጥሞላቸዋል።
ክብር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በንግግራቸው ባለሃብቶች በበጎ አድራጎት እና ፈጠራ የኦቪድ ኮንስትራክሽን ግሩፕን አርዓያነት እንዲከተሉ ጥሪ አቅርበዋል።
#PMOEthiopia