ኢትዮጵያና ቻይና የ161 ሚሊዮን ብር የድጋፍ ስምምነት ተፈራረሙ

ኢትዮጵያና ቻይና 161 ሚሊዮን ብር የአስቸኳይ ምግብ ድጋፍ ስምምነት ተፈራረሙ፡፡

የፋይናንስ ድጋፉ በኢትዮጵያ ለአስቸኳይ ጊዜ የምግብ እርዳታ የሚውል ሲሆን በሀገሪቱ በግጭትና በተፈጥሮ አደጋዎች ጉዳት የደረሰባቸውን የህብረተሰብ ክፍሎች ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ታውቋል፡፡

በስምምነቱ ወቅት በተካሄደው ውይይት በሁለቱ ሀገራት መካከል በሚካሄደው የኢኮኖሚ ትብብር በቀጣይ የቻይና ባለሀብቶች በኢትዮጵያ ኢንቨስት ለማድረግ ፍላጎት እንዳላቸው ተጠቁሟል፡፡

ቻይና ለኢትዮጵያ የቀላል ባቡር ፕሮጀክት የምትሰጠውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥልም ተመልክቷል፡፡

ስምምነቱን በገንዘብ ሚኒስቴር የኢኮኖሚ ትብብር ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ሰመሪታ ሰዋሰው እና በኢትዮጵያ የቻይና ኤምባሲ የኢኮኖሚና ንግድ አማካሪ ያንግ ዪሀንግ መፈራረማቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ አመላክቷል።

Share this Post