"ዛሬ ማለዳ 1686 ቤቶችን ለአቅመ ደካሞች እና የሃገር ባለውለታዎች እያስተላለፍን እንገኛለን።

በሁሉም ክፍለ ከተሞች በመተላለፍ ላይ የሚገኙት እነዚህ ቤቶች ደረጃችውን የጠበቁ እና መገልገያ እቃ የተሟላላቸው ሲሆን ለከፍተኛ ማህበራዊ ችግር የተጋለጡ አቅመደካማ ነዋሪዎች አዲሱን ዓመት በአዲስ ቤት በአዲስ ተስፋ በደስታ እንዲቀበሉ ያስችላቸዋል።

ይህ እንዲሳካ ከጎናችን በመቆም ራዕያችንን የተጋሩ ልበ-ቀና ባለሀብቶችን በከተማችን ነዋሪዎች ስም ላመሰግን እወዳለሁ።"

ከንቲባ አዳነች አቤቤ

Share this Post