09
Dec
2023
--------
አንዳችን የአንዳችን አካል ፣ አንዳችን የሌላችን ሃሳብና ጉልበት ሆነን ብዝሃነትን እና እኩልነትን በስራ አረጋግጠን የወደፊቷን ኢትዮጵያን እንገነባለን።
ዛሬ በጂግጂጋ ከተማ ያየነውም ይሄንኑ የሚያጠናክርልን ነው:: ወርቃማዋ ጂግጂጋ የአንድነታችንና እኩልነታችን መሰረት የሆነውን የብሄር ብሄረሰቦች ቀንን ስታከብር በድምቀት ፣ ተስፋን በሚያጭር ፣ የያዝነውን የብልፅግና ጉዞ እውን በሚያደረግ ፣ በሚያነሳሳ እና በሚያነቃቃ መንገድ መሆኑ በዓሉን ለየት ያደረገዋል።
ለጋራ ብልፅግና የተጋመደው ውጥናችን ፣ በጋራ ቃል ኪዳናችን እያፀናን ፣ እኩልነት እና አንድነትን በፅኑ መሰረት ላይ በመገንባት የኢትዮጲያ ልጆች ብልፅግናን እናረጋግጣለን!
በድጋሚ እንኳን አደረሳቹ አደረሰን !!