የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ በሦስት ወራት ብቻ ከ18 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰብ መቻሉን አስታወቀ


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ 2015 በጀት ዓመት የመጀመሪያው ሩብ ዓመት 18 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን አስታወቀ።

የቢሮው ኃላፊ አቶ ሙሉጌታ ተፈራ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ ቢሮው ባለፉት ሦስት ወራት 17 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር ገቢ ለመሰብሰብ አቅዶ 18 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ በመሰብሰብ የእቅዱ 106 ነጥብ 8 በመቶ በላይ ማሳካት ችሏል፡፡

አፈጻጸሙ ካለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር 33 ነጥብ 7 በመቶ መጨመሩን አስታውሰው፤ በበጀት ዓመቱ ለመሰብሰብ ከታቀደው አጠቃላይ ገቢ 26 ነጥብ 5 በመቶ የሚሸፍን መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

ገቢ ግብርን ለማሳደግ ብሎም አዳዲስ የገቢ አማራጮችን ለማስፋትና በዘላቂነት እየተሰራ ነው ተብሏል

Share this Post