የአዲስ አበባ ምክር ቤት 2ኛ አመት 3ኛ መደበኛ ጉባኤ የአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ ዋና ስራ አስፈፃሚን ጨምሮ የተለያዩ አስፈፃሚ አካላትን ሹመቶች በማጽደቅ ተጠናቋል፡፡

ምክር ቤቱ በአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ / አዳነች አቤቤ የቀረበለትን የተለያዩ አስፈፃሚ አካላትና ልዩ ልዩ ሹመቶችን አፀድቋል፡፡

በዚህም መሰረት

/ ጀማሉ ጀንበር

በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ የአረንጓዴ ልትማና የከተማ ውበት ቢሮ ኃላፊ

አቶ ቢኒያም ምክሩ

የአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ቢሮ ኃላፊ

አቶ አብርሃም ታደሰ

የአዲስ አበባ ከተማ የህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ቢሮ ኃላፊ

አቶ አደም ኑሪ

የአዲስ አበባ ከተማ የገቢዎች ቢሮ ኃላፊ

አቶ በላይ ደጀን

የአዲስ አበባ ከተማ የወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ

/ ሃቢባ ሲራጅ

የአዲስ አበባ ከተማ ቴክኒክና ትምህርት ስልጠና ቢሮ ሃላፊ

አቶ ካሳሁን ጎንፋ

የአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ ዋና ስራ አስፈጻሚ

/ እናትአለም መለሰ

የአዲስ አበባ ከተማ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ

አቶ አብዱልቃድር ሬድዋን የፋናንስ ቢሮ ኃላፊ

አቶ አያሌው መላኩን

የአዲስ አበባ አቤቱታ ሰሚ ጉባኤ ሰብሳቢ ሆነው በመሾም በምክርቤቱ አባላት ፊት ቀርበው ቃለመኀላ ፈፅመዋል::

Share this Post