ዛሬ ከ 2 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው 9 የአስልፓት መንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶችን አስመርቀን ለአገልግሎት ክፍት አድርገናል።

ፕሮጀክቶቹ ከ20 ኪሎ ሜትር በላይ ርዝመትና እስከ 43 ሜትር የጎን ስፋት ያላቸው ሲሆን የመንገዶቹ ግንባታ መጠናቀቅ የትራፊክ ፍሰቱን በማሳለጥ፣ የጉዞ ጊዜንና ወጪን በመቀነስ፣ የከተማውን ገፅታ በመቀየር፣ የስራ እድል በመፍጠር፣ የመንገድ ደህንነትን በማረጋገጥ እንዲሁም የከተማውን የማህበራዊ መስተጋብር በማሻሻልና ኢኮኖሚውን በማነቃቃት ረገድ ከፍተኛ ሚና የሚጫወት ይሆናል።

የመንገድ ፕሮጀክቶቹ ጀምሮ የመጨረስ፣ በገባነው ቃል መሰረት የማገልገል እና የህዝባችንን ጥያቄዎች በተጨባጭ እየመለስን መሆናችንን የሚያሳዩ ናቸው።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ

Share this Post