የአዲስ አበባ ከተማ ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ እናት-ዓለም መለሰ የ2015 ዓ.ም የምስጋናና ዕውቅና መረሀ-ግብርን ጨምሮ የ2016 አንደኛ ሩብ ዓመት የአፈጻጸም ግምገማ ውይይትን የመሩ ሲሆን በተዋረድ ከከተማ -እስከ ወረዳ የሚተገበር ቀጣይ የሥራ አቅጣጫም ሰጥተዋል ።
በዕውቅናና የዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ መረሀ-ግብሩ ላይ የኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ እናት-ዓለም መለሰ እንዳሉት ፤-በከተማ ደረጃ በቡድን በሚገልጽ ቅንጅታዊ እንቅስቃሴ እስከ ወረዳ ባለን መዋቅር በርካታ አበረታች የሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን ስራዎችን ያለፈውን ዓመት ጨምሮ አሁን በምንገኝበት አንደኛ ሩብ ዓመት በጋራ አከናውነናል ያሉት ሲሉ በአጠቃላይ የነበሩንን ጥንካሬዎች በተሻለ ማስቀጠል ከእያንዳንዳችን በነብስ ወከፍ የሚጠበቅ ሥፍራው የሚጠይቀን ኃላፊነት ነው ብለዋል ።
ባለሙያነትን በማካበትና የሚዲያ አማራጮቻችንን አሁን ካለን በላይ በማስፋት የህዝባችንን የመረጃ ጥም በማርካት ድልድይ ሆነን በሚፈለገው ልክ ልናገለግል ይገባልም ሲሉ የቢሮ ኃላፊዋ አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል ።
ቢሮው በስሩ ላሉ ተጠሪ የኮሙኒኬሽን ጽ/ቤቶች ባላፈው በጀት ዓመት ላሳዩት ጥቅል አፈጻጸም የምስጋናና የዕውቅና ሽልማት ሰጥቷል ፡፡
በምስጋናና ዕውቅና መረሀ-ግብሩ ላይ የቀድሞ የክፍለ ከተማ የኮሙዩኒኬሽን ጽ/ቤት ኃላፊዎች በነበሩበት ወቅት ላበረከቱት አስተዋጽኦ ሁሉ የዕውቅናና የምስጋና ሽልማት ተሰጥቷቸዋል ።