የ2016 የኢሬቻ በዓል እጅግ ደማቅ ፣ ሰላማዊ እና ትውፊቱን በጠበቀ መልኩ መከበሩን የቱለማ አባገዳ እና የኦሮሞ አባገዳዎች ህብረት ፀኃፊ አባገዳ ጎበና ሆላ ገልፀዋል::

በተለይም በአዲስ አበባ ከተማ የተከበረው የኦሮሞ ህዝብ የምስጋና በዓል የሆነው የኢሬቻ የሆራ ፊንፊኔ በዓል ከተማዋ ደምቃና ተውባ እንግዶቿን የተቀበለችበት መንገድ እንዳስደሰታቸው የገለፁት አባገዳ ጎበና ሆላ በዓሉ የአንድነት ፣ የፍቅር እና የወንድማማችነት መገለጫ መሆኑ በግልፅ የታየበት ነበር ብለዋል::

የዘንድሮው የኢሬቻ በዓል የሁሉም ኢትዮጵያዊያን መዲና በሆነችው አዲስ አበባ ከመቼውም ጊዜ በላይ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ታዳሚ ፍፁም ሰላማዊ እና ወንድማማችነት ጎልቶ በታየበት መልኩ መከበሩን ገልፀዋል::

የአዲስ አበባ እና የሸገር ከተማ ነዋሪዎች እንግዶችን በወንድማማችነት መንፈስ ተቀብለው ለማስተናገድ ላሳዩት ፍቅር ያላቸውን አድናቆት የገለፁት አባ ገዳ ጎበና ሆላ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በተለይም ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዓሉ ከምንጊዜውም በላይ ደማቅ እና ሰላማዊ ሆኖ እንዲከበር ላደረጉት አስተዋፅኦ ምስጋናቸውን አቅርበዋል::

Share this Post