የአዲስ አበባ ምክር ቤቱ የከተማ አስተዳደሩን ለ2016 ዓ.ም በጀት አመት የ140.29 ቢለየን ብር በጀት አፀደቀ፤

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የከተማ አስተዳደሩን 2016 / በጀት እቅድ መርምሮ ያፀደቀ ሲሆን

በበጀት አመቱ:-

=> ለመደበኛ በጀት ወጪዎች ብር 23,498,446,197.00

=> ለካፒታል ወጪዎች 69,336,835,072.00

=> ለመጠባበቂያ በጀት 5,300,000,000.00

---

ለክፍለ ከተሞች:-

=> መደበኛ በጀት ወጪዎች ብር 33,498,495,001.00

=> ለፒታል ወጪዎች 8,657,773,794.00 የመደበ ሲሆን፣

በጥቅሉ ለከተማ አስተዳደሩ 140,291,550,064.00 ብር በጀት ለመደበኛ፣ ካፒታልና መጠባበቂያ በጀት አፅድቋል፡፡

የበጀት እቅዱን ለምክር ቤቱ ያቀረቡት የአዲስ አበባ ከተማ ፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ አቶ አብድር ቃድር ሬድዋን እንደገለፁት አጠቃላይ አሁናዊ በጀቱ ከአምና ተመሳሳይ ወቅት ሲነፃፀር 40% እድገት እንዳለው ገልፀው የተያዘውን በጀት ለማሳካት ከታክስ ነክና ታክስ ነክ ካልሆኑ ገቢዎች፣ ማዘጋጃቤታዊ፣ መንገድ ፈንድ፣ የውጭ እርዳታ የውጭ ብድር ገቢን ታሳቢ ያደረገ መሆኑን ገልፀዋል።

ኃላፊው አክለው እንደገለፁት የገቢና ወጭ አፈፃፀምን ለማሳካት የኢኮኖሚውን እድገት ማስቀጠል፣ ምርታማነትንና ተወዳዳሪነትን ማሳደግ ከተማ አስተዳደሩ በቀጣይ በትኩረት የሚሰራበት ይሆናል ብለዋል።

Share this Post