የኢፌድሪ መንግስት እና የሶማሌላንድ መንግስት የፈረሙት የትብብር እና የአጋርነት መግባቢያ ሰነድ በተለያዩ ዘርፎች በቀጣይ ለሚኖር ግንኙነታቸው ማዕቀፍ የሚሆን ነው። ይህ የመግባቢያ ሰነድ የኢትዮጵያን የባህር በር የማግኘት ፍላጎት እውን የሚያደርግ፣ የባህር በር አማራጮችን የሚያሰፋ፣ የሁለቱን ወገኖች የፖለቲካ፣የዲፕሎማሲ፣ የፀጥታ እና የኢኮኖሚ ትብብር የሚያጠናከር ነው።
እንዲሁም ሰነዱ በፖለቲካ እና በዲፕሎማሲ ዘርፍ የሚኖራቸው ግንኙነት የሚጎለብትበትን አካሄድ የሚያካትት ነው። ይህ የመግባቢያ ሰነድ የኢትዮጵያ መንግስት በሰጥቶ መቀበል መርህ እና ለጋራ ጥቅም ከጎረቤቶቿ ጋር የመስራት ፍላጎት እና አቋሟን መልሶ የሚያፀና ነው። ይህ ሰነድ አዲስ የትብብር ምዕራፍ የሚከፍት እና ለአፍሪካ ቀንድ ትሥሥር የላቀ ፋይዳ ያለው ነው። እንዲሁም ሰነዱ ኢትዮጵያ በቀጠናው ሰላም እና ደህንነት የሚገባትን ሚና እንድትጫወት የተሻለ እድል የሚፈጥር ነው።
ለተጨማሪ መረጃ፦
YouTube https://www.youtube.com/channel/UCagI4q5d_EtvTsajRXWnFjA
Tik Tok= https://www.tiktok.com/@aacommu
Telegram https://t.me/AAcommu
Facebook https://www.facebook.com/profile.php?id=100066583024934...
Website https://cityaddisababa.gov.et