17
Jul
2023
ፕሮጀክቶቹ በ 410,217,800.ሚሊዮን ብር ወጪ የተደረገባቸው ሲሆን፣ ከ24ቱ ፕሮጀክቶች 7ቱ በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ "የመደመር ትውልድ" መፅሐፍ ሽያጭ በተገኘ ገቢ ለከተማችን ህፃናትና ወጣቶች የስፓርት ማዘወተሪያ ለመገንባት የተከተማ አስተዳደሩ ቃል ገብቶ የተረከበው ናቸው።
ጠቅላ ሚኒስትሩ አዲስ አበባን ለዛሬና ለነገው ትውልድ ምቹ ለማድረግ፣ በከተማችን ልጆች እንደ ልባቸው የሚቦርቁባት ፣ በየአካባቢያቸው በቂ የመጫወቻ እና ስፖርት ማዘውተሪያ ቦታ እንዲኖራቸው ለማድረግ ባበረከቱልን "የመደመር ትውልድ" መፃሀፍ ለከተማ አስተዳደሩ አደራ ሰጥተው በሦስት ወር ጊዜ ውስጥ 7ቱን የወጣት የስፖርት ማዘውተሪያ እና የህፃናት መጫወቻ በ110 ሚሊዮን ብር "ከመደመር ትውልድ" መፅሃፍ ሽያጭ በተገኘ ገንዘብ ተገንብተው ለአገልግሎት ክፍት ሆነዋል።
ሌሎቹ 17ቱ ፕሮጀክቶች ደግሞ የከተማ አስተዳደሩ ከ300 ሚሊዮን በላይ በሆነ ወጪ ተደርጎባቸው የተገነቡ ሲሆን፣ ይህም የከተማው ወጣቶችና ልጆች በአካል እና በአእምሮ የበለጸጉ ሆነው እንዲያድጉ ለማድረግ ከተማ አስተዳደሩ በትኩረት ለመስራቱ ማሳያዎች ናቸው።