ለቦረና ህዝብ ያሰባሰብነውን ከ250 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የአይነት እና የገንዘብ ድጋፍ ለክልሉ መንግስት አስረክበናል::

በተለያዩ ግዜያት ከህዝብ ጎን በመቆም የሚታወቁ የከተማችን ባለሃብቶች ያስተባበራችሁ አመራሮች እንዲሁም የህብረተሰብ ክፍሎች ለቦረና ህዝብ ላሳያችሁት አለኝታነት እና ፍቅር ከልብ አመሰግናለሁ::

በቀጣይም ችግሩን በዘላቂነት ለመቅረፍ የክልሉ መንግስት እየሰራቸው ያለውን ስራዎች ሁሉ የከተማ አስተዳደሩ እንደሚደግፍ ለማሳወቅ እወዳለሁ::

ከንቲባ / አዳነች አቤቤ

Share this Post