ለአቅመ ደካሞች፣ ለሃገር ባለውለታ አረጋዊያን፣ በዝቅተኛ ገቢ ለሚተዳደሩ የመንግስት ሠራተኞች እና ምንም ገቢ ሌላቸው ከ263 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ነዋሪዎች እንኳን አደረሳችሁ ብለን ማዕድ አጋርተናል።

በዚህ የበጎነት ተግባር ላይ የተሳተፋችሁ የከተማችን ባለ ሀብቶች፣ በጋራ ሆነን እምባ እያበስን ፍቅራችንን እና አክብሮታችንን ለህዝባችን መግለጽ ስለቻልን አመሰግናለሁ።

ፈጣሪ በወጣ እጥፍ አድርጎ ይመልስላችሁ!

ከንቲባ አዳነች አቤቤ

Share this Post