22
Jul
2023
ዛሬ ለከተማችን ነዋሪዎች ተጨማሪ ብስራት የሆኑ 3 የዳቦ ፋብሪካዎችን መርቀን አገልግሎት አስጀምረናል።
የዳቦ ፋብሪካዎቹ በዝቅተኛ ገቢ የሚተዳደሩ የከተማችን ነዋሪዎች ኑሮ በመደጎም ረገድ ትልቅ ድርሻ የሚኖራቸው ሲሆን በቀን እስከ 1 ሚልየን ዳቦ ያመርታሉ። በጥቅሉ በከተማችን ዕለታዊ የዳቦ ማምረት አቅምን ወደ 5.2 ሚልየን የሚያሳድጉ ናቸው።
የዳቦ ፋብሪካዎችን ከአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ጋር በመተባበር ገንብታችሁ ለአገልግሎት ያበቃችሁ አልኸይር የዳቦ ፋብሪካን ፣ ዩኒቲ የዳቦ ፋብሪካን እና ዮናን የዳቦ ፋብሪካን በከተማችን ነዋሪዎች እና በተጠቃሚዎች ስም ላመሰግን እወዳለሁ።