23
Sep
2022
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሁሉንም ክፍለ ከተሞችን በማሳተፍ 50 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጣ 1ሺ 195 ሰንጋዎች እና በጎች፣ 1ሺ 231 ኩንታል ደረቅ ምግብ፣ የዱቄትና ጥሬ እህል፣ 3ሺ 995 ሊትር ዘይት፣ ፍራሽ፣ አልባሳት እና የንጽህና መጠበቂያን ጨምሮ ሌሎች የሚውሉ ድጋፎችን በማሰባሰብ አስረክቧል።ድጋፉን ያስረከቡት የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ አቶ ሙሉጌታ ተፈራ አስተዳደሩ ለመከላከያ ሰራዊት ድጋፍ ሲያደርግ ለ3ኛ ጊዜ ሲሆን በመጀመሪያ እና በ2ኛ ዙር ከ110. 8 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገምት የአይነት ድጋፍ ማድረጉን ተናግረዋል።
የመከላከያ ሰራዊቱ የኢትዮጵያን ህልውና ለማስጠበቅና አሸባሪውን ቡድን የከፈተውን ጦርንት ለመቀልበስ በሚያደርገው ተጋድሎ በስንቅና በሞራል በመደገፍ ደጀንነታችንን አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል።ድጋፉን የተረከቡት የመከላከያ ሚኒስቴር የፋይናንስ ዳሬክቶሬት ዳይሬክተር ብርጋዴር ጀነራል ዘላለም ፈተና አስተዳደሩ ላደረገው ድጋፍም አመስግነዋል።