16
Oct
2023
በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ በ3ኛው ዙር በ90 ቀናት ከተሰሩ ሰው ተኮር ፕሮጀክቶቻችን መካከል የአቅመ ደካማ ቤቶች እድሳት ፣ አደባባዮችን የማስዋብና የማልማት ስራ እንዲሁም የወረዳ ህንጻ፣ ለስራ አጥ ወጣቶቻችን የሚሆኑ የመስሪያ ሼዶች እና የፖሊስ ጣቢያ ግንባታዎችን አጠናቅቀን ለነዋሪዎቻችን አገልግሎት እንዲሰጡ ክፍት አድርገናል።
ፕሮጀክቶችን በጥራት እና በጊዜ የማጠናቀቅ ባህል መጎልበት የታየበት ሲሆን ግንባታውን ያከናወናችሁ አልሚዎችን እና ያስተባበራችሁ አመራሮችን በነዋሪዎቹ ስም ላመሰግን እወዳለሁ።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ