30
Jun
2023
የዓለም ተሞክሮ እንደሚያሳየው ከተሞች ሲያድጉ በዙሪያቸው ያሉ አርሶአደሮችን እና ገጠራማ ቦታዎችን አካተው አብረው ያድጋሉ እንጂ ህይወታቸውን የሚመሩበት ገቢ እና የመኖሪያ ቦታ ታሳቢ ሳይደረግ ያላግባብ ከይዞታቸው አይፈናቀሉም።
በከተማችን አርሶአደሮች በይዞታቸው ላይ ተጠቃሚ እንዳይሆኑ፣ ደላሎችን ጨምሮ በተለያዩ አካላት ሲጭበረበሩ እና በይዞታቸው የመጠቀም ህጋዊ መብታቸው ሲነፈግ የቆየ ሲሆን ይህን ለማስቀረትና የአርሶ አደሮችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በርካታ የውይይት መድረኮች አካሂደናል። የአርሶአደሮችን መሰረታዊ ጥያቄዎች በመለየት መሻሻል ያለባቸውን የህግ ማዕቀፎች እና አሰራሮች አሻሽለናል።
በቀጣይም አርሶአደሮች በህግ የተሰጣቸውን ይዞታ የመጠቀምና ያለ አግባብ ከይዞታቸው ያለመፈናቀል መብታቸውን በማስከበር ከከተማዋ እድገት ጋር አብረው በማደግ የልማቱ አካል እንጂ ተፈናቃይ እንዳይሆኑ እንሰራለን።"
የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ