ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በቂርቆስ ክ/ከተማ 40 ቤቶችን መልሶ ግንባታ አስጀመሩ፡፡

 

ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በዛሬው እለት በቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 10 ጨርቆስ አካባቢ እጅግ የተጎሳቆሉ ሁኔታ ያላቸውን አርባ ቤቶች ሙሉ ለሙሉ አፍርሶ መልሶ በአዲስ መልኩ የመገንባት ሂደት አስጀምረዋል፡፡

ሄይኒከን ቢራ ፋብሪካ በበጎፍቃድ በትብብር በሚያስገነባው በዚህ ግንባታ ማስጀመርያ ላይ አስተያየታቸውን የሠጡት ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ እንደተናገሩት ከተማን ማልማት የመንግስት ሃላፊነት ብቻ አይደለም፤ ማህበራዊ ሃላፊነታቸውን በሚወጡ ተቋማትና ባለሃብቶች ጭምር እንጂ ብለዋል፡፡

ሌሎቻችንም በዚሁ ልክ ከመንግሥት ጋር በጋራ ለከተማችን ዕድገትና ለነዋሪዎቿ ብልጽግና ማሕበራዊ ኃላፊነታችሁን ለመወጣት እንድትዘጋጁ እናሳስባለን ብለዋል።

የሄኒከን ቢራ ዋና ስራ አስፈፃሚ ሁበርት ኢዝ በበኩላቸው በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚኖሩትን ነዋሪዎች ህይወት ለማሻሻል መስራት የኛም ሃላፊነት ነው ፤በመሆኑም በአጭር ጊዜ አጠናቀን ለተጠቃሚው እናስረክባለን፤ለዚህም ቁርጠኛ ነን ብለዋል፡፡

የቂርቆስ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ዘመኑ ደሳለኝም በበኩላቸው ቤቶቹን በሁለት ወራት ጊዜ ውስጥ አጠናቀን ለነዋሪው እናስረክባለን በማለት ቃል ገብተዋል፡፡

 

 

Share this Post