06
Oct
2023
ኢሬቻ የኦሮሞ ህዝብ ተፈጥሮን ውብ አድርጎ የፈጠረውን ፈጣሪ የሚያመሰግንበትና የሚያከብርበት፣ የተጣላ ጸቡን በይቅርታ የሚሽርበት፣የሰላም፣ የአብሮነት እና የአንድነት መገለጫ ነው።
የከተማችን ነዋሪዎች በአምስቱም በሮች የሚገቡ እንግዶችን ቤት ያፈራውን በመያዝ በፍቅር እየተቀበሉ ህብረ ብሔራዊ ወንድማማችነትንና እህትማማችነትን በተግባር በማሳየት አዲስ አበባ የኢትዮጵያ ተምሳሌት መሆኗን አስመስክረዋል።
ኢሬቻ የከተማችንን የቱሪስት መዳረሻነት እና ገቢ በማሳደግ ረገድ ትልቅ አስተዋኦ አለው ፤የከተማ አስተዳደራችንም በዓሉን ለመታደም የመጡ በርካታ የውጭ ሀገር ቱሪስቶችን በክብር እያስተናገደ ይገኛል::
የኢሬቻ ዕሴት ያልሆኑና መታየት የማይገባቸውን ድርጊቶች ከመፈጸም እየተቆጠብን በዓሉን በፍቅር፣ በአንድነትና በድምቀት እንድናከብር ጥሪዬን አስተላልፋለሁ ።
አባገዳዎች ፣ሀደ ስንቄዎች፣ ፎሌዎች ፣ መላው አመራራችን ፣ የጸጥታ አካላት ፣የሰላም ሠራዊት አባሎቻችን እና መላው የከተማችን ነዋሪ ላደረጋችሁት ሁሉ በከተማ አስተዳደራችን ስም ለማመስገን እወዳለሁ!
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ