17
Jul
2023
ከንቲባ አዳነች ባስተላለፉት መልዕክት በከተማችን በተመረጡ 140 የችግኝ መትከያ ቦታዎች ከ 4ሚሊየን በላይ ችግኞች እንተክላለን ያሉ ሲሆን በአገር አቀፍ ደረጃ በአንድ ጀምበር 500ሚሊየን ችግኞችን ተክለን እናሳካለን ብለዋል።
አክለውም በመርሃ ግብሩ ለመሳተፍ ለተገኙ የሀይማኖት አባቶች፣ ባለሀብቶች፣ የንግዱ ማህበረሰብ አባላት፣ አምባሳደሮች፣ ዲፕሎማቶች፣ ምሁራን ፣ የህክምና ባለሙያዎች፣ አባት አርበኞች፣ በተለያዩ ቦታዎች ችግኝ በመትከል ላይ ለሚገኙ የከተማዋ ነዋሪዎች በራሳቸውና በአስተዳደሩ ስም ምስጋና አቅርበዋል፡፡
ዛሬ የምንተክለው ችግኝ የነገ የመኖራችን ዋስትና እና የምግብ ዋስትናችንን የምናረጋግጥበት ከመሆኑም በላይ ኢትዮጵያውያን አንድነታችንን የምናሳይበትም ትልቅ ቀን ነውም ብለዋል፡፡
ከንቲባ አዳነች ለከተማው ነዋሪ ባስተላለፉት ጥሪ ሁሉም የከተማችን ነዋሪ በየአካባቢው ችግኞችን በመትከል አረንጓዴ አሻራውን ያሳርፍ ብለዋል።