ዛሬ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ በ60 ቀናት ተገንብተው የተጠናቀቁና ነባር የተለያዩ 57 ፕሮጀክቶች ተመረቁ ::

 

አድዋ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ፥ የምገባ ማዕከል : የተለያዩ ፓርኮች ፥ የክፍለ ከተማ የአስተዳደር ህንፃ ፧የስፖርት ማዘውተሪያ ማዕከላት ፥ 7 ፖሊስ ጣቢያዎች ፥ የአደባባይ ማስዋብ ፕሮጀክቶች፥ የዳቦ ፋብሪካና መሸጫ ሱቆች ዛሬ ከተመረቁ ፕሮጀክቶች ውስጥ ናቸው::

በፕሮግራሙ ላይ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ባደረጉት ንግግር ዛሬ የምንመርቀውን ጨምሮ በ2014 ዓ.ም ይዘናቸው የነበሩ 334 ፕሮጀክቶች በስኬት ማጠናቀቅ ችለናል ያሉ ሲሆን እነዚህ ብቻ ሳይሆን ደግሞ በህዝባችን ፤ በበጎ አድራጊ ባለሃብቶች ትብብር ደግሞ ሌሎች ከ300 በላይ ፕሮጀክቶች መሰራት ችለዋል ሲሉም ገልፀዋል፡፡

እንዲሁም ከንቲባ አዳነች ፕሮጀክቶችን በመገንባት ሂደት ፤ህዝቡ ከጎደሎው እያወጣ በየአካባቢው ተሳትፎው የማድረጉ ባህል እየተጠናከረ መምጣቱ በእጅጉ የሚያኮራ ነው ብለዋል፡፡

ከዝህ ቀደም እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል በሚል እሳቤ ብዙ ፕሮጀክቶች ተጀምረው ጥለው የተሄዱና የህዝብ ሃብት በማባከን ብዙ ጉዳት ደርሰዋል ያሉት ከንቲባ አዳነች ነገር ግን እነኚህን በየአካባቢው የተጀመሩ ፕሮጀክቶችን ለቅመን የህዝብ ሃብት ስለሆኑ ልዩ ትኩረት ሰጥተን በመስራት አጠናቀን ለህዝብ ጥቅም አውለናል ብለዋል፡፡

አሁንም ከለውጥ በፊት የተጀመሩ ውላቸውን ለማቋረጥ እንኳን ያላገኘናቸው ኮንትራክተሮች አሉ ያሉት ከንቲባዋ፤ ሃገር የምትገነባው በጋራ ነው ፥ ፕሮጀክቶች ስንጨርስም የምንጠቀምበት በጋራ ነው።

ባለሃብቶች የሚያድጉትም የሚለወጡት ህዝብ በተገቢው አገልግሎት ሲያገኝ ነው ሲሉም አፅንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።

እነዚህ ፕሮጀክቶች ትርጉማቸው ብዙ ነው በክ/ከተማው ተቋማት በተለያየ ቦታ ቢሮ ኪራይ ሲከፍሉ የነበረበት እና ህዝቡ ሲጉላላ የነበረበት ነው፡፡

ስለሆነም ህዝቡን አክብረን ልናገለግልበት ፤ ለህዝብ የገባነውን ቃል ልንተገብርበት ነው፤ ለህዝቡ ቀልጣፋ አገልግሎት ልትሰጡበት ይገባልም ብለዋል።

ለዚህ ፕሮጀክት ስኬት ፕሮጀክቱ በተጓተተበት ጊዜ በመድረስ የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎችን የጎደለውን በመሙላት ላደረገው አስተዋፅኦ እናመሰግናለንም በማለት ገልፀዋል፡፡

Share this Post