በመዲናችን እየተገነቡ ካሉ ፕሮጀክቶች ውስጥ ዘመናዊ የትራስፖርት ማዕከል፣ የየካ መኪና ማቆሚያ እና አዲስ አፍሪካ ኮንቬንሽን ማዕከልን ተዘዋውረን ጎብኝተን የግንባታ ሂደታቸውንም ገምግመናል:: በዚህም ዘመናዊ የትራስፖርት ማዕከል 63% ፣የየካ መኪና ማቆሚያ 66% እና አዲስ አፍሪካ ኮንቬንሽን ማዕከል 85% የግንባታ ደረጃ ላይ ደርሰዋል።

የህዝብ ሃብትን በቁጠባ በማስተዳደር በጥናት ላይ ተመርኩዘን ለችግሮች መፍትሄ ለመስጠት የጀመርናቸው ፕሮጀክቶቻችን በጥራትና በተያዘላቸው ጊዜ እንዲጠናቀቁ ተገቢውን ክትትል እያደረግን ለመኖር ምቹ የሆነች ከተማ መገንባታችንን አጠናክረን እንቀጥላለን::

ከንቲባ አዳነች አቤቤ

Share this Post