29
Jan
2023
በተለይም ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ማህበረሰብ የምንገነባቸው 240 ቤቶችን የያዙ ባለ 5 ወለል 6 ህንፃዎች፣ የአካባቢ ውበት አረንጓዴ ስፍራዎች ማራኪና አካባቢው መለወጥ በሚያስችል ሁኔታ እየተሰሩ ይገኛሉ፡፡ የሌማት ትሩፋት፣ የዳቦና የምገባ ግንባታዎች በመጠናቀቅ ደረጃ ላይ እንደሚገኙ ማየት ተችሏል፡፡
የአገልግሎት አሰጣጥ በማዘመን ብልሽት እና ሌብነትን ለመዋጋት መሰረታዊ የቴክኖሎጂና ዘመናዊ አሰራርን በመጠቀም ለማገልገል ዝግጅት ተደርጎ የተጠናቀቀው አዲሱ የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ጽህፈት ቤት ህንፃ የቃጠሎ አደጋ ቢያጋጥመውም በከፍተኛ ትኩረትና እልህ በአጭር ቀን ውስጥ መልሶ በተሻለ ሁኔታ ለመስራት ርብርብ እየተደረገ ነው።
በዚህ አጋጣሚ የህብረተሰቡም ሆነ የመንግስት ምንም አይነት ዶክመንት ለእሳት አለመዳረጉን ለማረጋገጥ ችለናል፡፡
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን አብዝቶ ይባርክ!!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ