13
Mar
2023
6 ባለ አራት ወለል የሆኑ 240 ቤቶችን ገንብተናል:: የረዥም ግዜ የመሰረተ ልማት ጥያቄ ላለባቸው የአርሶአደር የመኖሪያ አከባቢዎች የውሃ ፣ የመብራት እንዲሁም ሌሎች መሰረተልማቶችን ገንብተን ለአገልግሎት ክፍት አድርገናል::
ቅድሚያ ህዝቡን በሙስና ያስመረሩትን አካላት በህግ ቁጥጥር ስር በማዋል ሌብነትን ለማስቀረት እና አገልግሎት አሰጣጡ ከተማውን በሚመጥን ደረጃ እንዲሆን የዲጂታል አገልግሎት የሚሰጥ የአስተዳደር ህንፃ ገንብተን ዛሬ ለአገልግሎት ክፍት አድርገናል::
በዝቅተኛ ገቢ የሚተዳደሩ ነዋሪዎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ባለሃብቶችን በማስተባበር 6 ባለ አራት ወለል የሆኑ 240 ቤቶችን ገንብተን ለአከባቢው ነዋሪዎች አስረክበናል::
የረዥም ዘመን የመሰረተ ልማት ጥያቄ ላለባቸው የአከባቢው አርሶአደሮች የውሃ ፣ የመብራት እንዲሁም የሌሎች መሰረተ ልማቶች ተጠቃሚ እንዲሆኑም አስችለናል::
ህዝብን ለማገልገል ከመጣን በሌሎች ደባል ፍላጎቶች ሳንያዝ የህዝባችንን ጥያቄ ደረጃ በደረጃ በመመለስ ለመኖር ምቹ የሆነች ከተማ ለመገንባት እንሰራለን:: ይህ ብዙዎችን ተጠቃሚ ያደረገ ፕሮጀክት እንዲሳካ ማህበራዊ ግዴታቸውን ለተወጡ የከተማችን ባለሃብቶች በነዋሪዎች ስም ምስጋናዬን ላቀርብ እወዳለሁ::
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን አብዝቶ ይባርክ!!
ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ