የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ በ 90 ቀናት ሰውኮር ፕሮጀክት ከ80 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸውን ፕሮጀክቶች አስመርቆ ለአገልግሎት ክፍት አደረገ

የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ በ3ኛው ዙር በ90ቀናት ሰውኮር ፕሮጀክት ከ80 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸውን ፕርጀክቶች አስመርቆ ለአገልግሎት ክፍት አደረገ።

በዛሬው ዕለት በ90 ቀናት እቅድ ውስጥ ተገንብተው ከተመረቁት ፕሮጀክቶች መካከል:-በወረዳ ባለ 1 ወለል ህንጻ፤ የአቅመ ደካማ ቤቶች እድሳት፣በወረዳ 2 ዩኒሳ አደባባይን ማስዋብና ማልማት፣ በወረዳ 9 የመስሪያ ቦታ ሼድ እና በወረዳ 8 የመልካ ጨፌ ፖሊስ ጣቢያ ተጠቃሽ ናቸው።

ፕሮጀክቶቹን መርቀው አገልግሎት ያስጀመሩት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባና የስራ፣ኢንተርፕራይዝ እና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጃንጥራር አባይ: መንግስት የነዋሪዎችን የልማት ጥያቄ እና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት ቅድሚያ ሰጥቶ እየሰራ ነው ብለዋል። በዚህም በሰው ተኮር ፕሮጀክቶች ባለሃብቱን በማሳተፍ የመንገድ አካፋዮችና አደባባዮች የአቅመ ደካማ ቤቶች እና የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ሆነዋል ነው ያሉት።

በተለይም በዛሬዉ እለት የተመረቀው የወረዳ 8 ፖሊስ ጣቢያ የአካባቢው ሰላምና ደህንነትን ለማስጠበቅ እገዛ የሚያድርግ ነዉ ብለዋል።

አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ኦንዱስትሪ ዞን እና የጉምሩክ መግቢያ በር ከመሆኗ ጋር ተያይዞ መሰረተ ልማት የማስፈፋትና ሰው የኮር ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም ተናግረዋል።

የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር አበራ ብሩ በበኩላቸው አስተዳደሩ የግል ባለሃብቱንና በጎ-ፍቃደኛ የህብረተሰብ ክፍሎችን በማስተባበር በመጀመሪያውና በ2ኛው ዙር በ90ቀናት የተለያዩ የልማት ስራዎችን ሲሰራ መቆየቱን ጠቁመው በዛሬው እለትም በ3ኛው ዙር የ90 ቀናት እቅድ ከ80 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ በማድረግ የተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶችን አስመርቆ ለተጠቃሚዎች ክፍት ማድረግ መቻሉን ተናግረዋል።

በሰው ተኮር ፕሮጀክቶች የሚከናወኑ ተግባራት እቅዶችን በጥራት እና በጊዜ የማጠናቀቅ ባህል የጎለበተበት ስለመሆኑም ተናግረዋል። በቀጣይም በ3ኛው ዙር የተጀመሩ ስራዎች የማጠናቀቅ ስራዎች ይከናወናሉ ብለዋል።

Share this Post