በፈረንሳይ ፓሪስ የተከናወነውና በርካታ ሃገራት አባል በሆኑበት የዓለም የትምህርት ቤት ምገባ ጥምረት (School Meal Global Coalition) መድረክ ላይ ከተማችን አዲስ አበባ በሌሎች ሃገራት ልምድ የሚቀሰምባት ሆና በመመረጧ ትልቅ ኩራት ተሰምቶናል::

የትምህርት ቤት ምገባ ፕሮግራም ተጠቃሚ የሆኑ የአንደኛ ደረጃ ተማሪዎች ያሳዩት አበረታች ውጤት ፣ በምግብ እጥረት ምክንያት ከትምህርት ገበታ የሚቀር ተማሪ ቁጥር መቀነስ ፣ በምገባ ፕሮግራሙ ለእናቶች የተፈጠረው የስራ እድል ፣ ፕሮግራሙ ከከተማ ግብርና ጋር ማጣመር በመቻሉ እና የምገባ ማዕከል አቋቁማ በዘላቂነት ፕሮግራሙን በመምራት አዲስ አበባ ላሳየችው አርአያ የሚሆን ስራ ሌሎች ሃገራት ልምድ ሊወስዱባት እንደሚገባ በመድረኩ ላይ ተነስቷል።በቀጣይም ፕሮግራሙ የትውልድ ግንባታ አካል አድርገን ይበልጥ እያጠናከርን የምንሄድ ይሆናል::

Share this Post