"ዓለም አቀፍ የምርምር ተቋም ከሆነው World Resources Institute ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሚ/ር አኒ ዳሳጉፐታ እና የልዑካን ቡድናቸው አባላት ከሆኑት ሚስ ስቴንቲጃ ቫን ቬልድሆን 'የአውሮፓ አስተባባሪ' ፣ ሚስ ዋንጂራ ማታይ 'የአፍሪካ ዘርፍ' እና ዶ/ር አክሊሉ ፍቅረሰላሴ 'የአፍሪካ ቢሮ አስተባባሪ' ጋር በትብብር ልንሰራባቸው በምንችላቸው ጉዳዮች ዙሪያ ፍሬያማ ውይይት አድርገናል፡፡

በውይይታችንም አጋርነትን በማጠናከር ትብብራችንን ወደ ስትራቴጂክ እና የተቀናጀ ደረጃ ለማሳደግ እንዲሁም የከተማችንን ቀጣይ የልማት ስትራቴጂካዊ ፍኖት ለመንደፍ፣ የተቀናጀ መረጃን መሰረት ያደረገ የአመራር ስርዓት ለመዘርጋት የሚያስችል የመረጃ ቋት ለመገንባት፣ ከምንም በላይ ከተማችን አዲስ አበባ የነገ ተስፋችን የሆኑ ህጻናትን በእንክብካቤ ለማሳደግና ለትውልድ ግንባታ የምትመረጥ ከተማ ለማድረግ የሰነቅነውን ራዕይ ሁለገብ በሆነ መልኩ ሊደግፉን ተስማምተናል፡፡

ላሳዩን የትብብር ፈቃደኝነትና ተነሳሽነት እጅጉን እናመሰግናለን!"

ከንቲባ / አዳነች አቤቤ

 

Share this Post