18ኛው የብሔር ብሔረሰቦች ቀን ማጠቃለያ የባህል ፌስቲቫል በከተማችን ተከናውኗል።

ኢትዮጵያውያን በሕብረ ብሔራዊ ወንድማማችነትና እህትማማችነት ባስጌጧት የሁላችን ቤት በሆነችው አዲስ አበባ “ብዝሃነትና እኩልነት ለሃገራዊ አንድነት” በሚል መሪ ቃል 18ኛውን የብሄር ብሄረሰቦች ቀን ዛሬ ረፋድ ላይ አክብረናል።

ብዝሀነት ነባራዊ ሀቅ ፣ መዋቢያችን፣ መድመቂያችን መሆኑን ተገንዝበን ከሃገራዊ አንድነታችን ጋር አስተሳስረን በትጉሀን እጆች ወደ ብልፅግና እየገሰገሰች ያለችውን ኢትዮጵያን በሁላችን ትጋት ራዕይዋን እውን ማድረግ እንቀጥላለን!

 

ከንቲባ አዳነች አቤቤ

Share this Post