08
Dec
2023
--------
"ብዝኃነት እና እኩልነት ለሀገራው አንድነት" በሚል መሪ ቃል በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ አስተናጋጅነት እየተከበረ የሚገኘው የዘንድሮው የብሔር፣ ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ቀን ባለፉት ሶስት ቀናት በተለያዩ ስያሜዎች እና መርሃግብሮች ሲከበር ቆይቷል።
በዛሬው ዕለትም የ"መደመር ቀን" የሚል ስያሜ ተሰጥቶት የብሔር፣ ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ቀን ሲምፖዚየም በመካሄድ ላይ ይገኛል።
በሲምፖዚየሙ ላይ የኢፌዴሪ ፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አገኘው ተሻገር፣ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት አቶ ቴዎድሮስ ምህረት፣ የኢፌዴሪ ም/ቤት ም/ል አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ሎሚ በዶ፣ የክልሎች ርዕሳነ መስተዳድሮች፣ አፈ ጉባኤዎች፣ ከንቲባዎች፣ የሀይማኖት አባቶች፣ አባገዳዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና ሌሎች እንግዶችም ተገኝተዋል።